
ደብረ ብርሃን፡ መስከረም 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ አማራ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎች ላይ እየተወያዩ ነው፡፡
በመድረኩም የህልውና ዘመቻው በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ የምሁራን ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተመላክቷል።
ወራሪው እና አሸባሪው ትህነግ የኢትዮጵያን ሰላም እና እድገት ከማይፈልጉ የውጪ ኀይሎች ጋር በማሴር ኢትዮጵያን የማፍረስ የዘመናት ህልሙን ለማሳካት እየታተረ እንደሚገኝም በመድረኩ ተገልጿል።
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ንጉሱ ታደሰ ወራሪ ቡድኑ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ አማራን ማጥፋት አለብኝ በማለት በወረራቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ግፍ ፈጽሟል ብለዋል።
ዶክተር ንጉሱ ምሁራኑ የህልውና ዘመቻውን በመደገፍ በተለይ የዲፕሎማሲውን ሥራ በትኩረት በመስራት የራሳቸውን አስተዋፅኦ ሊያደርጉ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ:– ገንዘብ ታደሰ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ