
መስከረም 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ወራሪውና አሸባሪው የትህነግ ቡድን የዝርፊያና ሀገር የማፍረስ እኩይ ምግባሩን ከሚፋለሙት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኀይሉች ውስጥ ፋኖ አንዱ ነው። በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖች በድሬ ሮቃ ግንባር እየተፋለሙ ለሚገኙ የፋኖ አባላት ከ195 ሺህ ብር በላይ ወጭ የተደረገበት የስንቅ ድጋፍ አድርገዋል።
የድጋፉ አስተባባሪ አቶ ዳንኤል አደራ ፋኖ መደበኛ የሆነ መንግሥታዊ በጀት የሌለው መሆኑን በመረዳት የሚያደርጉትን ትግል ለማጠናከር ሲባል ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል፡፡አስተባባሪውም ድጋፉን ግንባር በመገኘት አስረክበዋል።
ሌላኛው የድጋፉ አስተባባሪ አቶ ቴዎድሮስ አያሌው በበኩላቸው “የትህነግ ወራሪ ቡድን ከምድረገጽ እስከሚጠፋ ትግላችንን አናቋርጥም” ብለዋል።
በተመሳሳይ የወሎ ቤተ አማራ ማኅበር አባላት ለድሬ ሮቃ ነዋሪዎች በተለይ ለወላድ እናቶች 133 ደርዘን ሳሙና፣ 100 ሜትር የዝናብና የፀሐይ መከላከያ ኬንዳና 17 ኩንታል ዱቄት ድጋፍ ያድጉ ሲሆን፣ ለፋኖ አባላትና ለተዋጊ አርበኞች ደግሞ 126 ሽርጥ ድጋፍ አድርገዋል።
ዘጋቢ፡- ካሳሁን ኃይለሚካኤል-ከድሬ ሮቃ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ