ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው በወሎ ግንባር ለተፈናቀሉ ዜጎች 100 ሚሊየን ብር መደቡ፡፡

885
ደሴ፡ መስከረም 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው በአሸባሪው ትህነግ ወረራ ሳቢያ በወሎ ግንባር ከቤታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ለድጋፍ የሚሆን 100 ሚሊየን ብር መመደባቸውን አስታወቁ።
ባለሀብቱ ትናንት እና ዛሬ ለተፈናቃዮች ለአልባሳትና ምግብ ነክ ግዥ 25 ሚሊየን ብር ወጪ አድርገዋል።
አቶ ወርቁ ለኢፕድ እንደገለፁት “ደብሊው ኤ” በተሰኘው ድርጅታቸው 100 ሚሊየን ብር መመደባቸውን ጠቁመው በንግዱ ማኅበረሰብ በተደረገ መዋጮ ደግሞ 40 ሚሊየን ብር ወጪ አድርገዋል።
በተመሳሳይም አሸባሪው ትህነግ በአፋር ግንባር ባደረሰው ጉዳት ለተፈናቀሉ ዜጎች 50 ሚሊየን ብር በግላቸው መለገሳቸው ይታወሳል።
እንደ አቶ ወርቁ ገለጻ፤ ልገሳው ጊዜያዊ ሲሆን በቀጣይ ዜጎች በቀያቸው እስኪቋቋሙ ድረስ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
አሸባሪውን ትህነግ እስከመጨረሻው ለመደምሰስ ወጣቶች ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከአማራ ክልል እና ከሌሎች ክልሎች ልዩ ኃይሎችና ሚሊሻዎች ጋር ተሰልፈው እንዲፋለሙም ጥሪ አቅርበዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleአሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን የሀገር ሰላም ስጋት እንዳይሆን እየቀበሩት መሆኑን በወሎ ግንባር የተሰለፉ የጦር መኮንኖችና የሠራዊት አባላት ገለጹ፡፡
Next article❝በቅርቡ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የድል ብሥራት እናሰማለን❞ የምእራብ እዝ አዛዥ ሜጄር ጄኔራል መሠለ መሠረት