አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን የሀገር ሰላም ስጋት እንዳይሆን እየቀበሩት መሆኑን በወሎ ግንባር የተሰለፉ የጦር መኮንኖችና የሠራዊት አባላት ገለጹ፡፡

320
ደሴ፡ መስከረም 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የ13ኛ ክፍለ ጦር አንደኛ ሬጅመንት አዛዥ ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት ሠራዊቱ በተሰማራባቸው የጦር ግንባሮች የአሸባሪውን ትህነግ ወራሪ ቡድን በመደምሰስና በመማረክ ላይ ነው፤ የሽብር ቡድኑ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እያደረሰበት ነው ብለዋል፡፡
የአሸባሪው ትህነግ ወራሪ ቡድን በደረሰባቸው አካባቢዎች በኅብረሰተቡ ላይ በርካታ ግፍ እየፈጸመ መሆኑን አዛዡ አንስተዋል፡፡ ኢትዮጵያን ከዚህ አሸባሪ ቡድን ለማላቀቅና በቀጣይም የሀገር ሰላም ስጋት እንዳይሆን እስከመጨረሻው እየቀበሩት መሆናቸውን አረጋግጠዋል ፡፡
የማዕከላዊ ዕዝ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክተር ተወካይ በየግንባሩ ሕዝቡ የሚጠብቀውን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ ሙሉ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል ፡፡
ሕዝቡ ለሠራዊቱ እያደረገ ያለው ድጋፍና ደጀንነት ሠራዊቱ የተጣለበትን ሀገራዊ ኀላፊነት በብቃት እና በውጤታማነት እንዲወጣ እያደረገው መሆኑንም ገልጸዋል ፡፡
ዘጋቢ፡- ባለ አለምዬ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበወረዳው ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች በዘላቂነት እንደሚያቋቁም የዳባት ወረዳ አስተዳደር ገለጸ።
Next articleባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው በወሎ ግንባር ለተፈናቀሉ ዜጎች 100 ሚሊየን ብር መደቡ፡፡