❝ጭና በሁለት መልኩ ታሪኳ ተፅፎ ይኖራል፤ አንደኛ የክፉውን የወያኔን ግፍ በመናገር ሁለተኛ የጭናን ሕዝብ ጀግንነት በመናገር❞ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

310
ደባርቅ: መስከረም 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥትና የመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች የጭና ነዋሪዎችን ጠይቀዋል።
የብልጽግና ጽሕፈት ቤት የሕዝብና ውጭ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አማካሪ ሚኒስትር ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ የደረሰው ጉዳት አሳዝኖናል፣ እንቅልፍ ነስቶናንልም ብለዋል። አሸባሪው ትህነግ ኢትዮጵያን ለመበታተን ተነስቶ ነበር፤ በእናንተ ጀግንነት ሕልሙ መና ሆኖ ቀርቷል ነው ያሉት። እናንተ እውነተኛ ጀግኖች ናችሁም ብለዋቸል።
ለዓመታት በኢትዮጵያውያን ጫንቃ ላይ ተቀምጦ ሰው እርስ በርሱ እንዲጠራጠር ሲሠራ መቆየቱንም ገልጸዋል። አካል ጉዳተኞችን ሳይቀር ገድሏል፣ ንጹሐንን ፈጅቷል፣ የሠራው በደል የጦር ወንጀል ነው፣ በሚጠየቅበት ጊዜ እንጠይቃለንም ብለዋል። እናንተ እውነተኛ ጀግኖች ናችሁ፣ ከየትም የመጣ አሸባሪ ቡድን መንደሬን አይደፍርም ብላችሁ፣ በመንደራችሁ እንዳይነግስ ኢትዮጵያውያንም እንዳይሰብራት ጋሻ ከለላ ሆናችኋልም ብለዋል። ኢትዮጵያን ጋሻ ከለላ ሆናችሁ አትርፋችኋታልም ነው ያሉት።
❝የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰማችሁ ሐዘን ተስምቶታል፤ የእናንተ ደም የእኔም ደም ነው ብሏችኋል፤ የእናንተን ለቅሶ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አልቅሷል ብለዋል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከእናንተ ጋር ነውና እንዳይከፋችሁ፣ የተበደላችሁትን ኢትዮጵያውያን ይክሷችኋል፣ ኢትዮጵያውያን እያሉ አትከፉም፣ አታዝኑም፣ የሚሰበረው ቅስም የጠላት ነው❞ ብለዋል። እጅ ለእጅ ተያይዘን የጎደለውን እንሞለዋለንም፣ የፈረሰውን እንሠራዋለን፣ የሞተውን እንስሳ እንተከዋለን ሲሉ ገልጸዋል። የጥፋት ቡድኑ ሁለተኛ የኢትዮጵያ ምድር ላይ እንዳይፈነጭ ዝቅ አድርገን እንቀብረዋለንም ብለዋል።
እናንተ የጠላትን ቅስም የሰበራችሁ ጀግኖች ናችሁና ኢትዮጵያ ታስባችኋለችም ብለዋቸዋል። እናንተ የኢትዮጵያ ጀግኖች ናችሁ፣ የኢትዮጵያዊነትን ክብር በጭና አስመስክራችኋልም ነው ያሉት።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ጽሕፈት ቤት አደረጃጀት ኃላፊ ተተካ በቀለ ❝እናንተ የምትፅናኑት በቃል ሳይሆን በፈፀማችሁት ጀብዱ ነው❞ ብለዋል። በጭና ሀገር የመበተን እሳቤውን ሕዝብ የመጨረስ እሳቤውን ማሰየቱንም ገልጸዋል። እናንተ ደግሞ የመጨረሻውን ጀግንነት ስላሳያችሁን በኩራት እንድንራመድ ስላደረጋችሁን በእጅጉ እናመስግናችኋለን ነው ያሉት።
አሸባሪው ቡድን የአንድነት፣ የኢትዮጵያዊነት ፀር ነው ያሉት አቶ ተተካ በእርግጠኝነት ከኢትዮጵያ አርቀን እንቀብረዋለን ብለዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ❝ወዳጅ የሚታወቀው በችግር ቀን ሲደርስ ነው፤ ጭና በሁለት መልኩ ታሪክ ታሪኳ ተፅፎ ይኖራል፣ አንደኛ የክፉውን የወያኔን ግፍ በመናገር ሁለተኛ የጭናን ሕዝብ ጀግንነት በመናገር ነው ❞ ብለዋል። ❝አይዟችሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎናችሁ ነው❞ ሲሉም ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“አሸባሪውን የትህነግ ወራሪ ቡድን መደምሰስ ብቻ ሳይሆን ትግራይ ላይ ተቀምጦ የባንዳነት ተግባሩን እንዳይወጣ ሴራውን ለመበጣጠስ የምሁራን ሚና ከፍተኛ ነው” አቶ አብርሃም አለኸኝ
Next articleበወረዳው ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች በዘላቂነት እንደሚያቋቁም የዳባት ወረዳ አስተዳደር ገለጸ።