
ባሕር ዳር፡ መስከረም 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) “ለፍትሕ እና ርትዕ መታገል የምሁራን ኀላፊነት ነዉ” በሚል መሪ ሐሳብ የአማራ ምሁራን በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ሁኔታ ላይ ውይይት እያካሄዱ ነው። ሽብርተኛው ትህነግ ሀገር ለማፈራረስ ቢታትርም እንዳልተሳካለት እና ኢትዮጵያውያን ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድ እንደሆኑ በውይይቱ ተነስቷል፡፡
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ አብርሃም አለኸኝ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን ወረራ በፈጸመባቸው የአማራ እና የአፋር ክልሎች የከፋ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥፋቶችን ማድረሱን ጠቅሰዋል።
ሽብርተኛው ትህነግ የፈጸመውን ወረራ ለመመከት የህልውና ዘመቻ በማወጅ በርካታ ድሎች እየተመዘገቡ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
“ሽብርተኛው የትህነግ ወራሪ ቡድን ጦርነት ቢከፍትብንም ጦርነቱ ክልላዊ አንድነት ያመጣ ነው” ብለዋል፡፡
ከጉዳቱ ለማገገም ምሁራን ያላሰለሰ ድጋፍ እያደረጉ ነው፤ ይህ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አንስተዋል።
አቶ አብርሃም እንዳሉት ሽብርተኛው ትህነግን ለመደምሰስ የምሁራን ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በቀጣይ በርካታ ሥራ ይጠበቅባቸዋል፤ አሽባሪው ትህነግ አማራን ብሎም ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሙከራ ቢያደርግም አይሳካለትም፡፡ ነገር ግን ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች መልሶ ለመገንባት የተያዙ ቦታዎችን ለማስለቀቅ እንዲሁም በቀጣዩ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ላይ ምሁራን ድርሻቸው የጎላ ነው ብለዋል።
ሽብርተኛው የትህነግ ወራሪ ቡድንን መደምሰስ ብቻ ሳይሆን ትግራይ ላይ ተቀምጦ የባንዳነት ተግባሩን እንዳይወጣ ሴራውን ለመበጣጠስ የምሁራን ሚና ከፍተኛ መሆኑን ኀላፊው ጠቁመዋል።
በውይይቱ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው የዩኒቨርስቲ ምሁራን እየተሳተፉ ነው።
ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ