
ባሕር ዳር: መስከረም 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በወረራው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አፋጣኝ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ ያለመ ውይይት በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
ውይይቱ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የችግሩን መጠን እና ስፋት ተገንዝቦ የተቀናጀ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርስ ያለመ ነው ተብሏል።
በውይይቱ የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል፣ የውኃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ስለሽ በቀለ (ዶ.ር) ፣ ብሄራዊ የአደጋ ስጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት አስተባባሪ ካትሪን ሱዚ (ዶ.ር) ጨምሮ የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።
በአማራ ክልል ብቻ 750 ኪሎ ሜትር በሚያካልል አካባቢ አምስት ዞኖች በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ ተፈጽሞብናል ያሉት የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ፈንታ ማንደፍሮ (ዶ.ር) ይህ በጦርነት ምን ማለት እንደሆነ ለእናንተ ማስረዳት አይገባም ነው ያሉት።
ዶክተር ፈንታ እንዳሉት በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ 4 ሚሊዮን ሕዝብ ለከፋ የሰብዓዊ ቀውስ ተዳርጓል፤ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሕዝብ ከመኖሪያ ቀየው ተፈናቅሏል፡፡



በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ ምክንያት የሰብዓዊ ድጋፎችን በሚመለከት ከበርካታ ረጂ ድርጅቶች ጋር ተደጋጋሚ ምክክሮችን አድርገናል ያሉት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ተግባራዊ ምላሹ ግን ከችግሩ ጋር የሚመጣጠን አይደለም ብለዋል። አሁንም ችግሩን በቅርበት የሚያውቁ ሁሉ በትብብር እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ