የዘመን መለወጫ በዓሉ በንፁህ ልቦና ወደ አዲስ ዓመት የሚሸጋገሩበት መሆኑን የሺናሻ ሽማግሌዎች ተናገሩ፡፡

417

ባሕር ዳር፡ መስከረም 18/2012 ዓ/ም (አብመድ) የጎሮ ሺናሻ ጋሪ- ዎሮ የዘመን መለወጫ የሕዝቦችን መስተጋብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሻግር የአብሮነት፣ የእርቅና የመቻቻል ተምሳሌት መሆኑን የብሔረሰቡ ሽማግሌዎች ተናግረዋል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የጎሮ ሺናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል ጋሪ- ዎሮ “በፍቅር፣ በሰላምና በአንድነት” በሚል መሪ መልዕክት ትናንት እና ዛሬ እየተከበረ ነው:: የብሔረሰቡ ሽማግሌዎች በዓሉ የተጣሉ የሚታረቁበት እና ወጣቶች የትዳር አጋሮቻቸውን የሚመርጡበት መሆኑን ተናግረዋል:: በዓሉ ቅሬታን ፈትቶ በንፁህ ልቦና ወደ አዲስ ዓመት የሚሸጋገሩበት እንደሆነም ተናግረዋል::

የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይዘሪት መስኪያ አብደላ የጋሪ ዎሮ በዓል ባህላዊ እሴት ሳይበረዝና ሳይከለስ ለትውልድ እንዲሸጋገር ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ኢዜአ እንደዘገበው በስፋት ታውቆና ለጎብኝዎች መስህብ ሆኖ በገቢ ምንጭነት እንዲያገለግል ለማድረግ እንደሚሰሩም ነው የተናገሩት፡፡

Previous article“ ግፋታ” የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል እየተከበረ ነው፡፡
Next articleበኩር መስከረም 19-2012 ዓ.ም ዕትም