ትምህርት ሚኒስቴር ለአማራ ክልል የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

205
ባሕር ዳር: መስከረም 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ትምህርት ሚኒስቴር በአማራ ክልል በአሸባሪው ትህነግ ለወደሙ ትምህርት ቤቶች መልሶ ግንባታ የሚውል 100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።
አሸባሪው እና ወራሪው የትህነግ ቡድን በአማራ ክልል በፈጸመው ወረራ ከ2 ሺህ 950 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኅላፊ ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ገልጸዋል። በጉዳቱም ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንዲርቁ ተገደዋል ብለዋል።
እብሪት የወለደው ድንቁርና ሕጻናት በወርኃ መስከረም እንዳይማሩ አድርጓል ያሉት የትምህርት ሚኒስትር ኢንጀነር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ.ር) ችግሩን የከፋ የሚያደርገው በጦርነቱ ወላጆቻቸውን ያጡ እና የተጎዱ ሕጻናት መኖራቸው ነው ብለዋል። ችግሩን ከስር ከስር መፍታት እና ማቃለል አሰፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል ያሉት ሚኒስትሩ በመደበኛ ከሚደረገው ድጋፍ በተጨማሪ እነዚህን ትምህርት ቤቶች ለመጠገን 100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበአሸባሪውና ወራሪው ትህነግ ከግብርና ሥራቸው የተስተጓጎሉ አርሶ አደሮችን ለማቋቋም እንደሚሠራ የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) አስታወቀ፡፡
Next articleጠላት ከየትኛውም አቅጣጫ ሊሰነዝር የሚችለውን ጥቃት በብቃት በመመከት የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት እንደሚያስከብሩ በልጉዲ ግንባር የተሰለፉ የጦር መሪዎች እና የሠራዊት አባላት ገለጹ፡፡