
መስከረም 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ነዋሪዎቹ በአካባቢው ባህል መሰረት በቀጠሮ ለቅሶ ተሰባስበው በሽብር ቡድኑ የተጨፈጨፉ ንጹሐን ሰማዕታትን ዘክረዋል፤ ሐዘናቸውንም ገልጸዋል።
በሰማዕታቱ መታሰቢያ ላይ የተገኙት ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ❝አሸባሪ ቡድኑን ከምድረ ገጽ ካላጠፋነው ዛሬ የተሰውት ነፍስ ይፋረደናል❞ ብለዋል።
እዚህ የተገኘነው ሐዘናችሁን ልንካፈል ነው ያሉት ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በጠላት ቡድኑ የተሰውትን ወገኖች ስናስታውሳቸው እንኖራለን ብለዋል። ❝ብቻችሁን አይደላችሁም እና ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ከጎናችሁ ስለሆኑ አትዘኑ❞ ነው ያሉት።

አሽባሪ ቡድኑ ሕዝብን ለማጥፋት ቆርጦ መነሳቱን በዚህ ከተማ የተጨፈጨፉት ወገኖች ማሳያ ናችው ብለዋል።
❝አሸባሪ ቡድኑን ከምድረ ገጽ ካላጠፋነው ዛሬ የተሰውት ነፍስ ይፋረዳል❞ ብለዋል ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል፡፡
አጥቂው ያጠቃን ይመስለዋል እንጂ አላጠቃንም፤ እኛም እጥፍ ድርብ አድርገን በልማትና ከተማዋን በማሳመር እናሳየዋለን ብለዋል። ❝ሁላችንም አንድ ሆነን የጠፋውን በማደስ ከተማዋን እንደገና ውብ እናደርጋታለን❞ ነው ያሉት።
የመንግሥት እና የመገናኛ ብዙኃን የሥራ ኀላፊዎች አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን የተሰው ቤተሰቦችን አስተዛዝነዋል።

ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ