የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ በሰሜን ወሎ ግንባር ከዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በግዳጅ አፈፃፀም ዙሪያ ተወያዩ።

657
መስከረም 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በግንባሩ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ ለምንም የማይበገረው መከላከያ ሠራዊት ከቀደምት የኢትዮጵያ ታሪክ በመነሳት ለህይወቱ ሳይሳሳ በሀገሪቱ ህልውና ላይ የተጋረጠውን አሸባሪ ኀይል ለመደምሰስ እያደረገ ያለውን ስኬታማ ኦፕሬሽን አድንቀዋል።
ጀነራል አበባው ሠራዊቱ በተደጋጋሚ የሚያስመዘግባቸው ድሎች የሽብርተኛውን ኀይል ለመደምሰስ አስተማማኝ ቁመና ላይ በመሆኑ ለላቀ ግዳጅ አፈፃፀምም የወትሮ ዝግጁነት አቅም የመፍጠሩ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ በበኩላቸው ሠራዊቱ ሕዝባዊነት ባህሪውን አስጠብቆ አሸባሪውን ኀይል አንገት እያስደፋ የወረራቸውን ቦታዎች በማስለቀቅ አኩሪ ታሪክ እየሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
❝አሸባሪው የትህነግ ቡድን በሕዝብ ላይ እያሳደረ ያለውን ግፍና በደል በመገንዘብ በአጭር ጊዜ እርምጃ በመውሰድ የተፈናቀለውን ማኅብረሰባችንን ወደ ቀየው እንዲመለስ ለማድረግ ግንባር ላይ ያለው ኀይላችን የጠላትን ቅስም እየሠበረ ነው❞ ብለዋል።
ተቋሙም በአሁኑ ወቅት ብቁ ሠራዊትን በማፍራት አስተማማኝ የዝግጁነት ምዕራፍ ማጠናቀቁን እንደገለጹ ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየመገናኛ ብዙኃን የሥራ ኀላፊዎች አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን በደቡብ ጎንደር ዞን ያደረሰውን ጉዳት እየተመለከቱ ነው።
Next articleበላይጋይንት ወረዳ የንፋስ መውጫ ከተማ ነዋሪዎች በአሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን በግፍ የተጨፈጨፉ ንጹሐን ሰማዕታት ዘከሩ።