
ደብረታቦር: መስከረም 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን በአማራ ክልል በፈጸመው ወረራ ዜጎችን ገድሏል፣ አፈናቅሏል፣ የግልና የመንግሥት ንብረት ዘርፏል፣ አውድሟል።
አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን በደቡብ ጎንደር ዞን ወረራ በፈጸመበት ወቅት ያደረሰውን ጉዳት የመገናኛ ብዙኃን የሥራ ኀላፊዎች እየተመለከቱ ነው።

አሸባሪ ቡድኑ በፈጸመው ወረራ ጉዳት የደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን፣ የወደሙ መሰረተልማቶችን እና የግለሰብ ሃብቶችን ይጎበኛሉ።
ምልከታቸውን በጉና በጌምድር ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ጀምረዋል።

ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ