
ደሴ: መስከረም 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ
ከሰሜን ወሎ ዞን ተፈናቅለው ኮምቦልቻ ከተማ ለተጠለሉ ወገኖች ነው ድጋፉን ያደረገው።
ለተፈናቃዮቹም 500 ኩንታል ዱቄት እና 2 ሺህ 500 ሊትር ዘይት ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉም 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር እንደሚያወጣ ተገልጿል።
ድጋፉም በኃይሌ እና ዓለም ኢንተርናሽናል ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ስም የተደረገ ነው ተብሏል።
አትሌቱ በአፋር ክልል በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ወረራ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቋል።
ዘጋቢ:- ከድር አሊ – ኮምቦልቻ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ