የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO) ልዑክ በአማራ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ ከርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ጋር እየተወያየ ነው።

114
ባሕር ዳር: መስከረም 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ክልል ርእስ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ሽብርተኛው የትህነግ ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል፡፡ በነዚህ አካባቢዎችም ከዚህ በፊት የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ በሰብል ላይ ያስከተለውን ጉዳትም ጠቅሰዋል፡፡
ርእሰ መሥተዳድሩ እንደገለጹት ሽብርተኛው ትህነግ በወረራቸው አካባቢዎች ዜጎችን እየገደለ ነው፤ ከቀዬአቸው እያፈናቀለ ነው፤ ሃብት እና ንብረት ዘርፏል፣ አውድሟል፣ ዜጎችም በቂ ምግብ እንዳያገኙ እያደረገ ነውም ብለዋል።
ድርጅቱ በእነዚህ አካባቢዎች አፋጣኝ የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያቀርብ ነው ርእሰ መሥተዳድሩ የጠየቁት፡፡ አሸባሪው ትህነግ በወረራቸው አካባቢዎች መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረስ አለመቻሉንም ጠቁመዋል። በውይይቱ ቀጣይ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ከተፈናቀሉ ወገኖች ጎን መሆኑን ለመግለጽና ድጋፍ ለማድረግ ዛሬ ኮምቦልቻ ከተማ ገብቷል።
Next articleአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ አሸባሪው ትህነግ በአማራ ክልል በፈጸመው ወረራ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።