“የመከላከያ ሠራዊትን ተቀላቅለን የእናት ሀገርን ጠላት ለመደምሰስ ቆርጠን ተነስተናል” ለመከላከያ የተመዘገቡ የገንዳ ውኃ ከተማ ወጣቶች

182
ገንዳውኃ: መስከረም 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የትህነግን የሽብር ቡድን ለመደምሰስ በሚደረገው የሕልውና ዘመቻ ወጣቱ በተደራጀ አግባብ አካባቢውን በንቃት ከመጠበቅ ባሻገር መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና በመውሰድ በግንባር እየተፋለመ ይገኛል።
በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውኃ ከተማ የሚገኙ ወጣቶችም የኢትዮጵያ ነቀርሳ የሆነውን የትህነግ ወራሪ ቡድን ለመደምሰስ የሁለተኛ ዙር መሰረታዊ ውትድርና ለመሰልጠን ተመዝግበው በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።
ወጣት መሰረት እምሩና ጌጤ ታረቀኝ በንጹሃን ላይ ኢሰብዓዊ ድርጊት እየፈጸመ ያለውን አሸባሪ ቡድን መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና በመውሰድ ለመደምሰስ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
አሸባሪዎቹ ትህነግና ሸኔ ጸረ አማራ ብቻ ሳይሆኑ ጸረ ኢትዮጵያ ናቸው ያለው ወጣት ክንዱ አበባው “የመከላከያ ሠራዊትን ተቀላቅለን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳውን የሽብር ቡድን በመደምሰስ ከአባቶቻችን በአደራ የተረከብናትን ሀገር ልንታደግና ዳግማዊ ዓድዋን ልናስመዘግብ ተነስተናል” ነው ያለው።
ሌላኛዋ ወጣት መሰረት ኩኒነር ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ያለውን አሸባሪ የትግራይ ወራሪ ቡድን ወታደራዊ ስልጠና በመውሰድ ለመደምሰስና የእናት ሀገርን ነጻነት ለማረጋገጥ ታጥቃ መነሳቷን ነው የገለጸችው።
የገንዳ ውኃ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ይግለጥ አበባው በአማራ ክልል ላይ ሂሳብ አወራርዳለሁ ያለውን የሽብር ቡድን ለመደምሰስ የከተማው ወጣቶች ከልዩ ኀይልና ከመከላከያ ሠራዊት ጋር ለመቀላቀል ያላቸው ወኔ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የእምነት ተቋማትን ሲያቃጥል፣ ንጹሐንን ዜጎችን ሲገል ሀብት ንብረታቸውን ሲዘርፍና ሲያፈናቅል የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ነን የሚሉ ምዕራባዊያን ሀገራት በዝምታ መታዘባቸውን ወጣቶቹ አውግዘዋል።
ዘጋቢ፡-ቴዎድሮስ ደሴ-ከገንዳ ውኃ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሚመራ ልዑክ ባሕር ዳር ገባ።
Next articleየኢትዮጵያዊነት ምስጢሩ ምን ይሆን?