በአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሚመራ ልዑክ ባሕር ዳር ገባ።

284
ባሕር ዳር: መስከረም 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ልዑካቸው በባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ኤርፖርት ሲደርሱ የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር እና ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ፈንታ ማንደፍሮ (ዶክተር) ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኅላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ልዑካቸው ባሕር ዳር የገቡት በሕልውና ዘመቻው ለተፈናቀሉ የአማራ ክልል ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ነው ተብሏል።
ምክትል ከንቲባዋ በቆይታቸው ከአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር እና ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኅላፊዎች ጋር ክልሉ በአሸባሪው ቡድን ወረራ በደረሰበት ጉዳት እና በዘላቂነት በሚደረጉ ድጋፎች ዙሪያ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የአዲስ አበባ ከተማ የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች፣ የከተማ አስተዳድሩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች እና የሲቭክ ማኅበራትና ተቋማት ተወካዮች የልዑኩ አባላት ናቸውም ተብሏል።
ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየአማራ ክልል ባለሃብቶች በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አደረጉ፡፡
Next article“የመከላከያ ሠራዊትን ተቀላቅለን የእናት ሀገርን ጠላት ለመደምሰስ ቆርጠን ተነስተናል” ለመከላከያ የተመዘገቡ የገንዳ ውኃ ከተማ ወጣቶች