የአማራ ክልል ባለሃብቶች በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አደረጉ፡፡

179
መስከረም 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ እና በደቡብ ጎንደር እና በሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎችና የአማራ ክልል ባለሀብቶች በአካል ተገኝተው ተመልክተዋል፤ ድጋፍም አድርገዋል፡፡
ባለሃብቶቹ ለተጎጂ ቤተሰቦች ከ11 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የገንዘብ እና የምግብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ የስንዴ ዱቄት፣ ዘይት እና ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰባቸው 56 ቤተሰቦች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 10 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ባለሀብቶቹ ሽብርተኛው ትህነግን በግንባር እየተፋለሙ ላሉ የፀጥታ አካላትም 1 መቶ ሰንጋዎችን ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች ያስከተለው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን ተዘዋውረው የተመለከቱት ባለሃብቶቹ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ቡሩክ ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleኢትዮጵያን በውጭ የሚወክሏት ሚሲዮኖች በአዲስ መልኩ ሊዋቀሩ ነው፡፡
Next articleበአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሚመራ ልዑክ ባሕር ዳር ገባ።