በእስራኤል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለህልውና ዘመቻ ከ340 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡

209
ባሕር ዳር: መስከረም 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትህነግ ኀይል እየፈጸመ ያለውን ወረራ ለመቀልበስ እየተካሄደ ያለውን የህልውና ዘመቻ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተለያዬ አግባብ እየደገፉ ነው፡፡
በእስራኤል “ለወገን ደራሽ ወገን” በሚል የተቋቋመው በጎ አድራጎት ማኅበር የተለያዬ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ማኅበሩ ለህልውና ዘመቻው የሚውል ከ340 ሺህ ብር በላይ በማሰባሰብ በባሕር ዳር ተገኝቶ ለአማራ ክልል ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴው አስረክቧል፡፡
በባሕር ዳር ከተማ በመገኘት ድጋፉን ያስረከቡት አቶ አወቀ ተገኘ ኢትዮጵያ የተጋረጠባትን ፈተና በድል እንድትወጣ ለማገዝ በእስራኤል ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የገንዘብ ድጋፉ እንደተሰበሰበ ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው ቡድን እስኪደመሰስ ድረስ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ጠቁመዋል፡፡
ድጋፉ ጅምር ነው ያሉት አቶ አወቀ ከዚህ የበለጠ በቀጣይ እንደሚያሰባስቡ ገልጸዋል፡፡ ድጋፉ በአጠቃላይ 344 ሺህ 596 ብር ነው ብለዋል፡፡
ሌሎች ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው የጠነቁት።
ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ምክትል ኀላፊ ወይዘሮ መሠረት አዱኛ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን እያደረጉት ያለው ድጋፍ የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡ ለተደረገው ድጋፍም ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
ድጋፉ የህልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ እና የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቸው ተመልሰው እስኪቋቋሙ ድረስ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የህልውና ዘመቻው በድል ይጠናቀቃል ያሉት ምክትል ኀላፊዋ በቀጣይ ኢትዮጵያ ልማቷን ለማፋጠን እና ሰላሟን አስጠብቆ ለመሄድ በውጪ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የበኩላቸውን ድርሻ እንዲያበረክቱ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article❝ከደብረ አሚን ጭና ተክለሃይማኖት አፀድ ሥር❞
Next articleአሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን የአቅመ ደካሞችን ቀለብ ሳይቀር ዘረፋ መፈጸሙን የገረገራ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።