
አዲስ አበባ: መስከረም 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የወጣት አደረጃጀቶችና ዩዝ ኢምፓወርመንት ያዘጋጀውና ከወጣቶች እስከ ታላላቅ ሰዎች ተሳትፈውበት ከመስከረም 3 እስከ መስከረም 15/2014 ዓ.ም ድረስ አምስት ሚሊዮን ደብዳቤዎች ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት የሚላክበት መርኃ ግብር ተጀመሯል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን እውነት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለማሳወቅ የነጩ ደብዳቤ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት በሚል በሀገሪቱ 1ሺህ 100 ከተሞች ሊካሄድ ነው።
በአዲስ አበባም በ113 ወረዳዎች የማስጀመሪያ መርኃግብር ተካሂዷል።
በአዲስ አበባም ዘማች ወጣት በሚል እየተካሄደ ባለው መድረክ ይሄው ፕሮግራም ተካሂዷል።
በደብዳቤ መላክ መርኃግብሩ ዓለም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን እውነት ይረዳል፣ የውጭ ጣልቃገብነት የማታስተናግድ ሀገር አለመሆኗንም ይገነዘብበታል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ:- እንዳልካቸው አባቡ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ