የብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል በመሠረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን የሠራዊት አባላት አስመረቀ።

151
መስከረም 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል በመሠረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን የሠራዊት አባላት ዛሬ አስመርቋል፡፡
ኢትዮጵያ የገጠማትን የህልውና አደጋ ተከትሎ የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተቀብለው በብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ማሰልጠኛ ማዕከል መሰረታዊ የውትድርና ስልጠናን ያጠናቀቁ የሠራዊት አባላት ናቸው የተመረቁት።
ተመራቂ ወታደሮች በውጊያ ቴክኒክ፣ በአካል ብቃት እንዲሁም በሌሎችም መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ በንድፈ ሐሳብ እና በተግባር የታገዘ ወታደራዊ ስልጠና ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
ተመራቂ የሠራዊት አባላቱ የሚሰጣቸውን ማናቸውም ግዳጆች በብቃት በመወጣት ሀገርን ከውስጥ እና ከውጪ ወራሪ ለመጠበቅ ያላቸውን ዝግጁነት ተናግረዋል።
በምርቃት ሥነ- ሥርዓቱ ላይ የሲዳማ ክልል ርእሰ መሥተደድር ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የጦር መኮንኖች መገኘታቸውን የዘገበው ኢብኮ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article❝ሕዝቡ መከላከያን ለመቀላቀል እያሳየው ያለው ተነሳሽነት ለጥፋት ኃይሎች የሞራል ሥብራት ነው❞ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ
Next articleየብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል በመሠረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን የሠራዊት አባላት አስመረቀ።