❝የደቡብ ክልል ሕዝብ ያደረገውን ድጋፍ የአማራ ሕዝብ ምንጊዜም አይረሳውም❞ ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር

212

ባሕር ዳር: መስከረም 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ)በአሸባሪው የትህነግ ወራሪ ኀይል ጥቃትና ዝርፊያ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍና ለህልውና ዘመቻው ያላቸውን ደጀንነት ለማረጋገጥ የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ርስቱ ይርዳው እና ልዑካቸው ባሕር ዳር ገብተዋል።

የደቡብ ክልል በአሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ኀይል ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ለህልውና ዘመቻው 25 ሚሊዮን ብር ለአማራ ክልል አበርክቷል። ለተፈናቀሉ ወገኖችም የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።

ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር የደቡብ ክልል ወንድም ሕዝብ ስላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። አሸባሪው ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች ንጹሐንን ጨፍጭፏል፣ የግለሰብ እና የመንግሥት ተቋማት ተዘርፈዋል፣ ወድመዋል ነገር ግን አሸባሪውን ቡድን አስወግደን እና እናንተን የመሰለ ወንድም ሕዝብ ይዘን መልሰን እንገነባዋለን ነው ያሉት። አሸባሪ ቡድኑን ኢትዮጵያ እንደማትፈርስ መስዋእትነት ከፍለን አሳይተነዋል ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ።

ግባችን ይህን ኀይል ከአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ትከሻ ላይ ማውረድ ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳደር አገኘሁ ጦርነቱ በቅርቡ በድል ይጠናቀቃል ብለዋል።

❝ደቡብ ክልል ሁሉም ሕዝብ በሰላም የሚኖርባት ትንሿ ኢትዮጵያ ናት❞ ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ድጋፋችሁን የአማራ ሕዝብ ምንጊዜም አይረሳውም ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየደቡብ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖችና ለሕልውና ዘመቻው 25 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።
Next article“የሶማሌ ሕዝብ በዚህ ትግል ብቻ ሳይሆን ከሶስት ሀገራት ጋር በሺህ ኪሎሜትሮች የሚያዋስኑ የሀገሪቱን ድንበር በመጠበቅ የሀገርን ሉዓላዊነት እያስከበረ ነው” የሶማሌ ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢንጅነር መሀመድ ሻሌ