የደቡብ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖችና ለሕልውና ዘመቻው 25 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

212

ባሕር ዳር: መስከረም 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው እና ወራሪው የትህነግ ቡድን በከፈተው ወረራ የሕልውና ዘመቻ ላይ ለሚገኘው እና ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰበት የአማራ ክልል የደቡብ ክልል አጋርነቱን ገልጿል። የደቡብ ክልል ሕዝብ የ25 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል። ከተደረገው የገንዘብ ድጋፍ ባለፈ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ምግብና ቁሳቁስ ተበርክቷል።

የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ርስቱ ይርዳው ዛሬ ጠዋት ባሕር ዳር ገብተው ከክልሉ ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር እና ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኅላፊዎች ጋር መክረዋል።

ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ርስቱ ይርዳው የሕልውና ዘመቻ የአማራ ክልል እዳ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያዊያን ሕልውና የመታደግ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው ያደረግነው እና በቀጣይም የምናደርገው ድጋፍ ችሮታ ሳይሆን ግዴታ ነው ብለዋል።

ጦርነቱ በመላው ኢትዮጵያዊያን ላይ የተከፈተ መሆኑን አውስተው ኢትዮጵያ ዳግም ወደቀደመ ክብሯ ትመለሳለች ነው ያሉት።

ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article❝የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ወጣቱ መከላከያ ሠራዊትን መቀላቀል ይገባዋል❞ ብርጋዴር ጀነራል አዳምነህ መንግሥቴ
Next article❝የደቡብ ክልል ሕዝብ ያደረገውን ድጋፍ የአማራ ሕዝብ ምንጊዜም አይረሳውም❞ ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር