❝የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ወጣቱ መከላከያ ሠራዊትን መቀላቀል ይገባዋል❞ ብርጋዴር ጀነራል አዳምነህ መንግሥቴ

524

መስከረም 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ የተጋረጠባትን የህልውና አደጋ ለመታደግ ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሠራዊትን መቀላቀል እንደሚገባቸው ብርጋዴር ጀነራል አዳምነህ መንግሥቴ ገልጸዋል።

ብርጋዴር ጀነራል አዳምነህ መንግሥቴ ለአሚኮ እንደተናገሩት የሀገር መከላከያ ሠራዊት መቀላቀል የተከበረና የላቀ የሙያ ባለቤት የሚያደርግ ነው።

ወጣቶች በተለያየ የሙያ ዘርፍ እንደሚሰማሩት ሁሉ በውትድርናው ዘርፍም የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

❝ወጣቱ ወደ መከላከያ ሠራዊት ቢቀላቀል የሚፈልገውን ዓላማ ለማሳካትም ሆነ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ለመላመድ ይጠቅመዋል፤ ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ጋር አብሮ በመሥራት የተለያዩ ተሞክሮዎችን በመቅሰምም የተሟላ ሰው ያደርጋል❞ ነው ያሉት።

ወጣቱ የውትድርና ሙያን ካልተቀላቀለ ሀገርን ለማፍረስ ከውስጥም ሆነ ከውጪ ሊመጡ ለሚችሉ ኃይሎች ባሪያ ለመሆን በር ይከፍታል ነው ያሉት። ወጣቱ ኢትዮጵያ የራሷን ታሪክ ጠብቃ፣ ታፍራና ተከብራ እንድትኖር የማድረግ ግዴታም ጭምር እንዳለበት ነው ብርጋዴር ጀነራሉ የተናገሩት። ወጣቱ ይህን እንዳያደርግ ተላላኪዎች ስላሉ ተላላኪዎችን በአጭሩ ማስቀረት እንደሚጠበቅም አሳስበዋል።

❝ጠላትን ለመከላከልና የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የሀገር መከላከያ ሠራዊት መቀላቀል ወሳኝ ነው❞ ብለዋል።

ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ርስቱ ይርዳው ባሕር ዳር ገቡ።
Next articleየደቡብ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖችና ለሕልውና ዘመቻው 25 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።