
ባሕር ዳር: መስከረም 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ በአሸባሪው የትህነግ ወራሪ ኀይል ጥቃትና ዝርፊያ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍና የሽብር ቡድኑን እየተፋለመ ላለው የወገን ሠራዊት ያላቸውን ደጀንነት ለማረጋገጥ ነው የተገኙት።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አሸባሪውና ዘራፊው የትህነግ ወራሪ ኀይል በአማራና በአፋር ክልል ባደረገው ወረራ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለዋል፤በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችም ለከፋ ችግር እየተጋለጡ ነው።
ኢትዮጵያዊያንም የሽብር ቡድኑን ሀገር የማፍረስ ተግባር በመመከትና ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ በማድረግ አጋርነታቸውን እያሳዩ ነው።
የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተደድር ርስቱ ይርዳው ባሕር ዳር የተገኙትም የክልላቸው ሕዝብ ከአማራ ሕዝብ ጎን መቆሙንና አሸባሪው ትህነግ እስኪደመሰስ ድረስ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ለማረጋገጥ ነው።
ዘጋቢ:- ስማቸው እሸቴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m