በድንጋይ ስድስት ክላሽ የማረኩት የድሬ ሮቃው ጀግና።

1051

ደሴ፡ መስከረም 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ስማቸው ሲራጅ ዲቢል አሊ ይባላሉ፡፡ በሀብሩ ወረዳ 024 ድሬ ሮቃ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው፡፡ ከሰሞኑ አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን ወደ ቀበሌያቸው ለመግባት ሲሞክር ቀበሌያቸውን ባለማስደፈር ታላቅ ጀብዱ ሰርተዋል፡፡

በሚኖሩበት ድሬ ሮቃ ቀበሌ ግንባር ላይ በመሰለፍ አንድ የአሸባሪው ቡድን አባል በወገን ጦር ላይ ጥቃት ለመፈፀም ሲሞክር በድንጋይ አንገቱን ብለው የያዘውን ክላሽ ማርከውታል፡፡ ከዚያም ሌሎች አምስት የአሸባሪው ቡድን አባላት ጓደኛቸውን ለማንሳት ሲመጡ አምስቱንም በመግደል የያዙትን አምስት ክላሽ በመማረክ በአጠቃላይ 6 ክላሽ ከአሸባሪው ትህነግ ወራሪ ቡድን መማረክ ችለዋል፡፡

በሃይማኖቴ እና በኢትዮጵያዊነቴ አልደራደርም የሚሉት አቶ ሲራጅ ወጣቱ የሀገሩን ሰላም እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን በርካታ ሕዝብ አሰልፎ ድሬ ሮቃን ለመያዝ ቢመኝም በቀበሌው ነዋሪዎችና በመከላከያ ሠራዊት ጥቃት ህልም ሆኖበት ወደመጣበት ተመልሷል ብለዋል፡፡

የቀበሌው ዋና አስተዳዳሪ ሸህ ሀሰን ከረሙ አሸባሪ ቡድኑ እኛን አልፎ እንዲሄድ አንፈቅድለትም፣ በቀጣይም ለሀገራችን መስዋእትነት እንከፍላለን ብለዋል፡፡

ዘጋቢ:– ተመስገን አሰፋ – ከድሬ ሮቃ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየኢትዮጵያ የ2013 ክራሞት
Next articleየደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ርስቱ ይርዳው ባሕር ዳር ገቡ።