❝ጦርነቱ ችግርና ፈተና ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንን የበለጠ እንደብረት ያጠነከረ መልካም አጋጣሚ ፈጥሯል፤ በዚህም የአንድነት መንፈስ ድል እየተመዘገበ ነው ❞ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም

179

ደሴ: መስከረም 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በወሎ ግንባር የሚገኘው የጸጥታ ኀይል ከከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር አዲስ ዓመትን አክብሯል።

በመርኃግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ብናልፍ አንዱዓለም እንዳሉት አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች በፈጸመው ወረራ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት አስከትሏል።

ጦርነቱ ችግርና ፈተና ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንን የበለጠ እንደብረት ያጠነከረ መልካም አጋጣሚ እንደፈጠረም ገልጸዋል። በዚህም የአንድነት መንፈስ ድል እየተመዘገበ መሆኑን አንስተዋል።

የወሎ ሕዝብ ከሠራዊቱ ጎን ተሰልፎ ላሳየው ድጋፍ እና ተጋድሎ ምስጋና አቅርበዋል።

የሀገሪቱን ልማት ለማፋጠንና ወደ ልማት ለመዞር ጦርነቱን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቀቅ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አብርሃም አለኸኝ የሀገርን ህልውና ለማስቀጠል የኢትዮጵያ ጀግኖች ዋጋ ከፍለዋል። በዚህ ወቅትም ሀገሪቱ የገጠማትን ፈተና በድል ለማጠናቀቅ ሠራዊቱ ከፍተኛ ጀብድ እየፈጸመ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት እና የየክልሎች የጸጥታ ኀይል በመቀናጀት የተጀመረውን የማጥቃት እርምጃ ሕዝቡ ደጀንነቱን በማጠናከር መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“የኢትዮጵያ ነፃነት ከልጅ ልጆች የሚተላለፍ የማይሸራረፍ እንደነበረ የሚቀጥል መሆኑን ለዓለም በድጋሜ እናሳያለን” የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ
Next articleየኢትዮጵያ የ2013 ክራሞት