የመቄት ወረዳ ከአሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ሙሉ በሙሉ ነጻ ሆነ፡፡

408
መስከረም 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን በመቄት ወረዳ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል፡፡ የተራረፈው የቡድኑ ርዝራዥም በደብረ ዘቢጥ፣ በአግሪት፣ በፍላቂትና በገረገራ ተለቅሞ ከተሞቹ መደበኛ እንቅስቃሴአቸውን ጀምረዋል፡፡
አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን አሁን ላይ በወገን ጦር በጋሸና እየደረሰበት ያለውን ከፍተኛ ድብደባ መቋቋም አቅቶት ወደ ኋላ እየፈረጠጠ መሆኑን የግንባሩ የጦር መሪዎች አስታውቀዋል፡፡
በዓልን በጦርነት እናሳልፋለን ብለን ብናስብም አሸባሪውና ወራሪው የትህንግ ቡድን የደረሰበትን ጥቃት መቋቋም ባለመቻሉና አካባቢው ሙሉ በሙሉ ነጻ በመውጣቱ አዲሱን ዓመት በድልና በደስታ እያሳለፉን ነው ብለዋል የግንባሩ የጦር መሪዎች፡፡
ዘጋቢ፡- ቡሩክ ተሾመ—ከገረገራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ አዲስ ዓመትን ከሠራዊቱ ጋር ለማክበር ማይጠብሪ ግንባር ገቡ።
Next article“የኢትዮጵያ ነፃነት ከልጅ ልጆች የሚተላለፍ የማይሸራረፍ እንደነበረ የሚቀጥል መሆኑን ለዓለም በድጋሜ እናሳያለን” የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ