የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ አዲስ ዓመትን ከሠራዊቱ ጋር ለማክበር ማይጠብሪ ግንባር ገቡ።

435
ባሕር ዳር፡ መስከረም 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የ2014 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ከሠራዊቱ ጋር ለማክበር ማይጠብሪ ግንባር ተገኝተዋል።
በማይጠብሪ ግንባር ከሠራዊቱ ጋር በዓልን ለማክበር የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ፣ ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሌትናል ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ የመከላከያ ኅብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሜጄር ጄኔራል ዘውዱ በላይ፣ የምእራብ እዝ እና የማይጠብሪ ግንባር አዛዥ ሜጄር ጄኔራል መሠለ መሠረት ጨምሮ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተገኝተዋል።
የሠራዊት አባላት ተልዕኳቸን በላቀ ብቃት በመወጣት በአዲሱ ዓመት በሀገራችን አስተማማኝ ሠላም እናሰፍናለን ብለዋል። ሕዝባችን ያሳየንን ከፍተኛ ድጋፍ የሞራል ስንቅ አድርገን በአዲሱ ዓመት ለሕዝባችን ታላላቅ የድል ብሥራቶችን ለማሰማት እንዘጋጅም ብለዋል።
ዘጋቢ:-ታርቆ ክንዴ-ከማይጠብሪ ግንባር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article❝አዲሱ ዓመት ፈተናዎቻችን ሁሉ በድል ተሻግረን የኢትዮጵያን ብልጽግና የምናይበት እንደሚሆን እምነቴ የፀና ነው❞ ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር
Next articleየመቄት ወረዳ ከአሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ሙሉ በሙሉ ነጻ ሆነ፡፡