ኢትዮጵያ በለተሰንበት ግደይ አማካኝነት የመጀመሪያውን ሜዳሊያ አገኘች፡፡

239

ባሕር ዳር፡ መስከረም 18/2012 ዓ/ም (አብመድ) በኳታር ዶሃ እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ10 ሺህ ሜትር የመጀመሪያውን የብር ሜዳሊያ አስመዝግባለች፡፡

ትናንት ምሽት በተካሄደው የሴቶች የ10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ለተሰንበት ግደይ ለኢትዮጵያ በውድድሩ የመጀመሪያውን የብር ሜዳሊያ ስታስመዘግብ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ሰንበሬ ተፈሪ 6ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡

ለተሰንበት ግደይ 30 ደቂቃ ከ21 ሰከንድ ከ23 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው ሁለተኛ የወጣችው፡፡ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷና ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ሲፋን ሀሰን በአንደኛነት ውድሩን አጠናቅቃለች፡፡

በውድድሩ ኬንያዊቷ አግኔስ ትሪፖ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች፡፡ ከቀናት በፊት በተደረገ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ተወዳዳሪዎች በነበረው ከባድ ሙቀት ውድድሩን ማቋረጣቸው ይታወሳል፡፡

Previous articleየሰሀላ ሰየምት ወረዳ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች ሰልፍ እያካሄዱነው፡፡
Next articleየመስቀል በዓል በዩኔስኮ መመዝገቡ የጎብኚዎችን ቁጥር እንዳሳደገው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ፡፡