
አዲስ አበባ፡ ጳጉሜን 05/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የድል ቃልኪዳን ብስራት ቀን አስመልክተው በትዊተር የማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
“የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ” በሚል ማኅበረሰብ ውስጥ ነው ያደግነው፤ ቃል ኪዳን የዓለም ህልውና የተመሠረተበት ሥርዓት ነው። ሰው ከሰው፣ ሰው ከአካባቢው፤ አካባቢ እርስ በርሱ ተጠባብቆና ተግባብቶ የሚኖረው በቃል ኪዳን ነው ብለዋል።
“ድል የገቡትን ቃል በማክበር፣ ለቃል ታምኖ በመሥራትና ቃልን በተግባር በመግለጥ የሚገኝ ነው። ቃል ማክበር ካለ የድል ብሥራት አለ። ለኢትዮጵያ የገባነውን ቃል ኪዳን አድሰንና አክብረን፣ የኢትዮጵያን ድል እናበሥራለን” ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
መንግሥትና ሕዝብ የሚኖሩት በቃል ኪዳን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደ መንግሥትና እንደ ሕዝብ ለገባናቸው ቃል ኪዳኖች ታማኞች ከሆንን ሀገር ሰላም፣ ምቹና ባለጸጋ ትሆናለች ብለዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ