“በጀግንነት ረገድ ያካበትነውን ወረት ለችግር ማለፊያ፣ ለውጤት ማትረፊያ፣ ለላቀ ማሸነፊያ አቅም እንዲሆነን በጥበብ ልንጠቀምበት ይገባል” አቶ ደመቀ መኮንን

133
አዲስ አበባ፡ ጳጉሜን 04/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በጀግንነት ረገድ ያካበትነውን ወረት ለችግር ማለፊያ፣ ለውጤት ማትረፊያ፣ ለላቀ ማሸነፊያ አቅም እንዲሆነን በጥበብ ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡
አቶ ደመቀ ዛሬ በአዲስ አበባ በተከበረው የጀግንነት ቀን መድረክ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ኢትዮጵያ በተገባደደው ዓመት የደረሱባትን ጫናዎች ተቋቁማና ያጋጠሟትን ፈተናዎችን ማለፍ የቻለችው ያፈራቻቸው ጀግኖች ልጆች በመኖራቸው ነው ብለዋል፡፡
አሁን ታሪክ የሚሠራበት ወቅት ነው፤ በምሥራቅና በምእራብ፣ በደጀንና በግንባር፣ በመላ ሀገሪቱ ሴቶች እና ወንዶች ጀግኖች ተነስተዋል፤ ሁሉም ሀገራዊ የጀግንነት ተግባር በመሥራት ላይ በመሆናቸው ኢትዮጵያ ከፍ ብላ ትኖራለች ብለዋል አቶ ደመቀ፡፡
“ጀግንነት ለኢትዮጵያውያ በሐሳብም በምግባርም እንግዳ አይደለም፤ ከቤት እስከ ዓለም መለያችን ነው፤ በየዘመኑ በጋራ እና በጀግንነት ጠላቶቻችንን አሸንፈናል” ብለዋል፡፡
ጀግኖቻችንን በማክበር እና በማስተባበር በኩል ያሉብንን ችግሮች ግን ሊናርማቸው ይገባል ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ዛሬ በጀግንነት ቀን መድረክ ላይ ባስተላለፉት መልእክት፡፡ ኢብኮ እንደዘገበው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ለመከላከያ ሠራዊት ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ።
Next article“ነፃነትን ተቀዳጅተን የምናከብረው ድርብ በዓላችን ነው” የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳዳሪ አሸተ ደምለው