
ባሕር ዳር፡ መስከረም 18/2012 ዓ/ም (አብመድ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰሀላ ሰየምት ወረዳ መሸሀ ከተማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡
ሰልፉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና ምዕመኖቿ ላይ እየደረሱ ያሉ በደሎችን የሚያወግዝና በጥፋተኞች ላይ መንግሥት ተጠያቂነትን እንዲያሰፍን የሚጠይቅ ነው፡፡
ፎቶ፡- የሰሀላ ሰየምት ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት