የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ለመከላከያ ሠራዊት ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ።

213
አዲስ አበባ: ጳጉሜን 04/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) የሥራ ኀላፊዎችና አባላት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ16 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል።
በዚህ ወቅት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው መከላከያ ሠራዊቱ የሀገርን ሉዓላዊነት እንዳይደፈር ምትክ የሌለውን ህይወት እየገበረ መሆኑን ገልጸው የኤጀንሲው የሥራ ኀላፊዎችና አባላትም ለኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት በፈቃደኝነት የአንድ ወር ደምወዛቸውን ለግሠዋል ብለዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ኤጀንሲው በተሰጠው ሀገራዊ ተልዕኮ በሕግ ማስከበር እርምጃው በተለያየ አግባብ እስከ ህይወት መስዋእትነት አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝና በቀጣይም የኤጀንሲው አባላት ግንባር ድረስ ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን ዋና ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ በበኩላቸው ቀንና ሌሊት ሀገርን ለሚጠብቀው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የኤጀንሲው የሥራ ኀላፊዎችና አባላት ስላበረከቱት ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ መረጃ ያሳያል፡፡
ኢዜአ እንደዘገበው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleኮሚሽኑ ከ4 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡
Next article“በጀግንነት ረገድ ያካበትነውን ወረት ለችግር ማለፊያ፣ ለውጤት ማትረፊያ፣ ለላቀ ማሸነፊያ አቅም እንዲሆነን በጥበብ ልንጠቀምበት ይገባል” አቶ ደመቀ መኮንን