
ባሕር ዳር: ጳጉሜን 04/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን አሜሪካ በኬንታኪ ግዛት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለመከላከያ ሠራዊት፣ ለልዩ ኃይል፣ለሚሊሻና ፋኖ ከ536 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ የሕክምና ቁሳቁስ ነው ድጋፍ ያደረጉት።
በሰሜን አሜሪካ በኬንታኪ ግዛት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተወካይ አቶ በላይነህ ሽታየ እንደገለጹት በሕልውና ዘመቻ ለሚፋለሙት የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ልዩ ኃይል፣ሚሊሻና ፋኖ ለሕክምና አገልግሎት የሚውል የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል። ሕይወት እየሠጡ ለሚገኙ የጸጥታ አካላት የሚደረገው ድጋፍም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የልዩ ኃይል የጤና ኃላፊዎችም በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያን ለሕልውና ዘመቻ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረጉ ነው ብለዋል።
ኃላፊዎቹ በሕልውና ዘመቻው የኢትዮጵያነት ትብብር የታየበት ነው፤ የጸጥታ ኃይሉም አሸባሪውና ወራሪውን የትህነግ ቡድን በመደምሰስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደስታ ለማብሰር ጠንክሮ እየሠራ ነው ብለዋል። ድጋፉም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፦ አዳሙ ሽባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ