“አሸባሪው የትህነግ ቡድን ወደ ደቡብ ወሎ ዞን ለመግባት ውጊያ ቢከፍትም ሽንፈትን ተከናንቦ ተመልሷል” የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰይድ መሐመድ

289
ደሴ፡ ጳጉሜን 04/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰይድ መሐመድ በወቅታዊ ጉዳዬች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። አሸባሪው እና ወራሪው የትህነግ ቡድን ወደ ደቡብ ወሎ ዞን ለመግባት ከአንድ ወር በላይ ውጊያ መክፈቱን የገለፁት አስተዳዳሪው በተሁለደሬ እና በወረባቦ ወረዳ በተወሰኑ ቀበሌዎች በመውረር ጥፋት መፈፀሙን ገልጸዋል። በተሁለደሬ 028 ቀበሌ እና በወረባቦ ወረዳ 018 ቀበሌ ሽንፈትን ተከናንቦ ተመልሷል ብለዋል።
ከ358 በላይ ሰርጓ ገቦች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ አቶ ሰይድ ጠቅሰዋል።
ሕዝቡ ለህልውና ዘመቻው በከፍተኛ ደረጃ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም አመላክተዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን ነዋሪዎች ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከ151 ሚሊየን ብር በላይ ለህልውናው ዘመቻው የቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።
አዲስ ዓመት በዓልን ስናከብር የተፈናቀሉ ወገኖች በመደገፍና የዘማች ቤተሰቦችን በመንከባከብ ልናከብረው ያገባል ነው ያሉት። ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ2014 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው፡፡
ዘጋቢ፡- አንዋር አባቢ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበወሎ ግንባር የተሰለፉ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በአሸባሪው እና ወራሪዉ የትህነግ ቡድን ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማድረሳቸው ተገለጸ።
Next article“ቢከፋት ነው እንጅ በደሉ ቢመራት፣ ልጆቿን አስትቶ መታጠቅ ያማራት”