
ባሕር ዳር፡ ጳጉሜን 04/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ወጣቶች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ልዩ ኃይልን እየተቀላቀሉ መሆናቸውን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ አህመድ ሐሰን አስታውቀዋል፡፡
እንደ ዋና አስተዳዳሪው ገለጻ በብሔረሰብ አስተዳደሩ የሚገኙ ዕድሜያቸው ለውትድርና የደረሱ ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የልዩ ኃይል አባል በመሆን የውጭና የውስጥ ጠላቶችን ለመመከት ዝግጁ ናቸው፡፡
አሸባሪው ትህነግ በከፈተው ጦርነት እና ባደረሰው ውድመት ወጣቶች በቁጭት ተነሳስተው የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ልዩ ኃይል አባል እየሆኑ ነው ብለዋል፡፡
ወጣቶች ወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ሁኔታን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ልዩ ኃይል አባል ለመሆን እየተመዘገቡ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡
አቶ አህመድ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሥራ ኀላፊዎች ስለ ሀገር ሉዓላዊነት መከበር እና የወጣቶች ሚና ግንዛቤ ፈጠራ ሥራ እየሠሩ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ልዩ ኃይል አባል ሲሆኑ ለእናት ሀገር የሚከፈለው ትልቅ መስዋእትነት እየከፈሉ መሆኑን በማሰብ እንዲመዘገቡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዋና አስተዳዳሪው በርካታ ወጣቶች የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን የከፈተውን ጦርነት ለመመከት ወደ ግንባር እየሄዱ ናቸው ብለዋል፤ አካባቢያቸውንም በንቃት እየጠበቁ መሆኑን እና ለህልውና ዘመቻው ሁለንተናዊ ድጋፍ እያደረጉ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ