
ባሕር ዳር፡ ጳጉሜን 04/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ የሚከበረውን የጀግንነት ቀን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት፣ “ሀገር በራሷ ቆማ፣ ራሷን ችላ፣ የራሷን ዕድል እንድትወስን ሁሉም ዓይነት ጀግኖች ያስፈልጓታል” ሲሉ ገልጸዋል።
“ጀግንነት የታጋይነት፣ የጽናት እና የአሸናፊነት ውጤት ነው። ጀግንነት መልከ ብዙ ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የጦር፣ የግብርና፣ የሳይንስ፣ የንግድ፣ የዕውቀት፣ የኪነ-ጥበብ፣ የመንግሥት ሥራ፣ የአገልግሎት ሰጪ፣ ወዘተ ጀግኖች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።
አንዱ ጀግንነት ያለ ሌላው እንደማይኖር የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ “ሀገር በራሷ ቆማ፣ ራሷን ችላ፣ የራሷን ዕድል እንድትወስን ሁሉም ዓይነት ጀግኖች ያስፈልጓታል።” ብለዋል።
ሀገር የምትጎዳው ጀግኖች በጎደሉበት መስክ እንደሆነም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስገንዝበዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ