“ትምህርት ቤቶችንና ሆስፒታል ማውደም በጦር ወንጀልኝነት መታየት አለበት” አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ

318
አዲስ አበባ፡ ጳጉሜን 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ሕወሓት “ትምህርት ቤቶችንና ሆስፒታሎች ላይ እያደረሰ ያለው ውድመት እጅግ አስነዋሪና በጦር ወንጀለኝነት መታየት ያለበት ድርጊት ነው” ሲል አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ተናገረ፡፡
“ማን ከማን ጋር እንኳ እንደተጋጩ የማያውቁ ህጻናትን ትምህርት ቤት ማውደም በምን ይገላጻል?” በማለት ነው በምሬት የጠየቀው፡፡
አትሌቱ በአማራ ክልል በዋግ ኸምራ ዞን ፃግብጂ ወረዳ በዳስ ጥላ ለሚማሩ ሕጻናት ያስገነባው ትምህርት ቤት በመውደሙ እጅግ እንዳዘነም ነው የገለጸው፡፡
አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ለኢዜአ እንደገለጸው ትምህርት ቤቱን ለመገንባት ከገንዘብ ወጪ በላይ በርካታ ውጣ ውረዶችን እንዳሳለፈ የሚገልጸው አትሌቱ፤ የትምህርት ቤቱ መውደም በአካባቢው ማኅበረሰብ ቁስል ላይ እንጨት እንደመስደድ ይቆጠራል ነው ያለው፡፡
አትሌቱ ያስገነባውን ጨምሮ በአካባቢው በርካታ ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎች መውደማቸውን ጠቅሶ፤ ይህም የአሸባሪው ሕወሓትን “የክፋት ጥግ ያሳያል” በማለት አስረድቷል፡፡
በየትኛውም ዓለም በሚካሄዱ ጦርነቶች ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎችን ዒላማ ማድረግ የጦር ወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑንም አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ተናግሯል፡፡
ትምህርት ቤቱም ከአምስት መቶ በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ሕጻናት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleአሸባሪው የትህነግ ቡድን በከፈተው ወረራ በአማራ ክልል ከ4 ሚሊዮን በላይ ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚሹ ተገለጸ።
Next articleበወልቃይት ጠገዴ ልዩ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ድል የተቀዳጁት የጸረ ሽምቅ ኀይል አባላት ጠላት ሳይጠፋ ወደቤታቸው ላይመለሱ ተማምለዋል።