በወምበርማ ወረዳ የሽንዲ ከተማ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡

586

ባሕር ዳር፡ መስከረም 18/2012 ዓ/ም (አብመድ) በአማራ ክልል ምዕራበ ጎጃም ዞን የሽንዲ ከተማ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡

የሰልፉ ዓላማ በቤተ ክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍና መከራ ማውገዝ እና ድርጊቱ እንዲስተካከል መጠየቅ ነው፡፡

በቤተ ክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ በደል የፈጸሙ አካላት በህግ እንዲጠየቁም ነው ምዕመናኑ እና የሀይማኖት አባቶች በሰላማዊ ሰልፉ የጠየቁት፡፡

“የቤተ ክርስቲያንን ህልውና መጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት ነው!፤ በቤተ ክርስቲያን እና በምዕመናን ላይ የሚፈጸመው ግፍና መከራ ሊቆም ይገባል” የሚሉና ሌሎችም መልዕክቶች በሰላማዊ ሰልፈኞቹ እየተስተጋቡ ነው፡፡

በአማራ ክልል ከመስከረም 4/2012 ዓ.ም ጀምሮ ባለሉት ተከታታይ ሳምንታት በቤተ ክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍና መከራ የሚያወግዙ እና ድርጊቱ እንዲስተካከል የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎች እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡

በሰላማዊ ሰልፉ የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ተሳትፈዋል፤ በቤተ ክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ እየደረሰ ያለውን ድርጊትም አውግዘዋል፡፡

ፎቶ፡- በወምበርማ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት

Previous articleበጋዝጊብላ ወረዳ አስከተማ የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ሰልፍ አካሂደዋል፡፡
Next articleየሰሀላ ሰየምት ወረዳ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች ሰልፍ እያካሄዱነው፡፡