❝መልካምነት በመስዋእትነታቸው ብዙ ለሆኑልን ለመከላከያ ሠራዊት አባላት እና ቤተሰቦቻቸው❞ ዶክተር አሕመዲን መሐመድ

195

ደሴ: ጳጉሜን 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አሕመዲን መሐመድ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው እንዳሉት አረንቻታ ሚዲያ ኮምቦልቻ ለሚገኙ የጀግናው መከላከያ ሠራዊት አባላት ቤተሰቦች ለበዓል መዋያ ያሰባሰበውን ድጋፍ አስረክቧል።

ለመከላከያ ሠራዊት አባላት ቤተሰቦች የተደረገውን ድጋፍ የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት ርክክብ መፈጸሙን ዶክተር አሕመዲን ገልጸዋል።

❝ከሃዲው የሕወሓት ሽብርተኛ ቡድን ጥቅምት 24 የጀግናው መከላከያ ሠራዊት ላይ በፈፀመው ግፍ ተጎጂ የሆኑ ቤተሰቦች መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳታችሁ ጉዳቱ፣ ሐዘናችሁ ሐዘኑ ነውና ሁሌም ከጎናችሁ ነን። ይህንን ድጋፍ ላሰባሰባችሁና ድጋፉን ላደረጋችሁ ሁሉ ምስጋና ይገባችኋል❞ ነው ያሉት።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሸህ እንድሪስ መሐመድ 100 ሺህ ብር ለአጣዬና አካባቢው ተፈናቃዮች ማቋቋሚያ መለገሳቸውን አመላክተዋል። ❝ሀገራችን የምትቀየረው እንደዚህ አይነት ቅንና መልካም ሰዎች ሲበዙ ነውና ሁላችንም ለመስጠት እጃችን የሚዘረጋ ይሁን❞ ብለዋል።

መልካምነት የአንድ ቀን ስራ ብቻ ሳይሆን የህይወት ዘመን መመሪያችን መሆን አለበት ያሉት ዶክተር አሕመዲን መልካምነት ለጀግናው እና የሕዝብ ደጀን ለሆነው መከላከያ ሠራዊታችን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article❝አሸባሪው ትህነግ የኢትዮጵያ ጠላቶች በአምሳያቸው ጠፍጥፈው ያበጁት ቡድን ነው❞ ዶክተር የሻምበል አጉማስ
Next articleቺርቤዋ ናሲ 30 ጌርክ 2013 ም.አ