
አዲስ አበባ: ጳጉሜን 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ድጋፉን የገቢዎች ሚኒስቴር የሕግ ተገዥነት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዘመዴ ተፈራና የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ እና የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዋና ዳሬክተር ገረመው ገርጂ በመከላከያ ሚኒስቴር በመገኘት አስረክበዋል፡፡
ተቋማቱን በመወከል የተናገሩት የሕግ ተገዥነት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዘመዴ ተፈራ ❝የትህነግ አሸባሪ ቡድን በሙሉ ዓይናችን እንኳን ለማየት የምንሳሳለትን የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ከጀርባው ወግቷል❞ ብለዋል።
በአማራና አፋር ክልል ሕዝቦች ላይም በዓለም ላይ ታይቶ የማይታወቅ ግፍ ፈፅሟል፤ ሆኖም ግን ይህ አሸባሪ ቡድን በጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ በክልል ልዩ ኀይልና ሚሊሻ አባላት እየተደመሰሰ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
አሸባሪውን ቡድን በአጭር ጊዜ እስከነ አስተሳሰቡ ለመቅበር የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ለአሁኑ የ11 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድረገናል፤ በቀጣይም ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው እንዳሉት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማቱ የሕዝብን ሀብት ለሕዝብ በሚል መርህ በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክኒያት የተፈናቀሉና ቤት ንብረታቸው ለወደመባቸውን ወገኖች ድጋፍ እንደተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም በአፋርና በሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ ተጎጂዎችን እንደሚደግፉም አስታውቀዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጅ በበኩላቸው የተደረገው ድጋፍ ኢትዮጵያዊነት በተግባር የታየበትና ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ደግሞ ትልቅ የሞራል ትጥቅ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው የትህነግ ቡድን በአጭር ጊዜ ተደምስሶ ፊታችንን መደ ልማት እንድናዞር ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበትን ኀላፊነት እንዲወጣም መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m