“አረመኔውና ጨፍጫፊው ትህነግ በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ በርካታ ንፁሃንን ጨፍጭፏል” አቶ ግዛቸው ሙሉነህ

670

የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት።

“የጀግኖቻችንን የተቀናጄ ጥቃት ሲቀምስ፣ በየጫካው እየተፋለሙት ያሉትን ጀግኖችን መቋቋም ያልቻለው ወራሪ በየቤታቸው የነበሩ አዛውንቶችን፣ ህፃናትንና እናቶችን በያሉበት መንደርና ሰፈር በመግባት፣ ቀሳውስትን ቤተ ክርስትያን ውስጥ ገብቶ የፍጥኝ በማሰር ጨፍጭፏቸዋል። የትግራይ ወራሪ ኃይል ቀደም ሲል በሰሜን ወሎ፣ በአፋር ክልል የፈፀመውን አይነት ዘግናኝ ጭፍጨፋ በሰሜን ጎንደር በዳባት ወረዳ በጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ በድጋሜ ፈፅሟል። ይህ ሰይጣናዊ ቡድን ከወረራቸው አካባቢዎች በአፋጣኝ ግብዓተ መሬቱ እስካልተፈፀመ ድረስ ሌሎች ጭፍጨፋዎችን እንደሚፈፅም ግልፅ ነው።

በጥላቻ የናወዘውና ጭፈጨፋን የዕለት ተዕልት ተግባሩ ካደረገው የትግራይ ወራሪ አድማስ የነካ በደል፣ ሰቆቃና የግፍ ፅዋ ሕዝባችንን ለመታደገ ፍጥነታችንን ጨምረን ማርሻችንን ቀይረን ከያለበት ግብዓተ መሬረቱን በመፈፀም ሕዝባችን ልንታደግ ይገባል።

ሚዲያዎቻችንም ይሄንን እውነት ዓለም እንዲያውቀውና ከወራሪውና ጨፍጫፊው ጋር በምናደርገው ትግል አብረውን እንዲቆሙና ድርጊቱንም እንዲያወግዙት በፍጥነት መዘገብና ቦታው ድረስ በመሄድም ሁኔታውን ማስረዳት ይገባናል።

በንፁሃን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አሰቃቂ ጭፍጨፋ የትግራይን ወራሪ ቡድን ግብዓተ መሬቱን በማፋጠንና ለሕዝባችን ዳግም ስጋት እንዳይሆን በማድረግ ደማቸውን እንደምንመልስ ጥርጥር የለውም። የትግራይን ወራሪ ኃይል ከየገባበት እየመታን ባለንበት ወቅት የቤተሰብና የወገንን ሀዘን የምንጠግነው በትግራይ ወራሪ ኃይል መቃብር ላይ ይሆናል!!!!

Previous articleአሸባሪው እና ወራሪውን የትህነግ ቡድን ከሠራዊቱ ጋር በመሆን ለመታገል ዝግጁ መሆናቸውን የደብረ ዘቢጥ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
Next articleከተለያዩ የሰሜን ወሎ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት ያለመ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው።