
ባሕር ዳር፡ ጳጉሜን 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትህነግ ቡድን በአማራ ክልል በፈጸመው ወረራ ዜጎችን ገድሏል፣ አፈናቅሏል፣ ሃብት ዘርፏል ብሎም አውድሟል፡፡
የአማራ ክልል መንግሥት ተፈናቃዮችን ለማቋቋም በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ድጋፍ እንዲያደርጉ የድጋፍ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡ በስዊድን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተፈናቃይ ወገኖችን መልሶ ለሟቋቋም ለቀረበው ጥሪ ፈጣን ምላሽ መስጠታቸውን የአማራ ክልል መንግሥት ገልጿል፡፡
ኢትዮጵያውያኑ አስተባባሪ ኮሚቴ በማቋቋም 29 ሺህ 165 የአሜሪካ ዶላር በመሰብሰብ “አማራ ሪሊፍ ፈንድ ፎር IDP” በሚል በተከፈተው የባንክ ሒሳብ ቁጥር ገቢ አድርገዋል ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ በአሸባሪው ትህነግ ወረራ የተፈናቀሉ ወገኖቻቸውን ለመደገፍ ስለ ሰጡት ፈጣን ምላሽ የአማራ ክልል መንግሥት ምስጋና አቅርቧል፡፡
ተፈናቃዮቹ በዘላቂነት እስኪቋቋሙ ድረስ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የክልሉ መንግሥት በስዊድን ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በላከው የምሥጋና ደብዳቤ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በአዳሙ ሺባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ