በእስራኤል ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለህልውና ዘመቻው ከ14 ሽህ ዶላር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡

164
ባሕር ዳር፡ ጳጉሜን 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) “አማራን እናድን ኢትዮጵያን እንታደግ በቅድስት እስራኤል” በሚል መሪ መልዕክት በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ገቢ ማሰባሰቢያ አካሂደዋል፡፡
አሸባሪው የትህነግ ቡድን በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተውን ወረራ ለመመከት የሚደረገውን የሕልውና ዘመቻ ለመደገፍ በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የሚያደርጉትን የገንዘብ ድጋፍ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ድጋፍ ሲያደርጉ እንደቆዩ ጠቁመው አሁን ደግሞ “አማራን እናድን ኢትዮጵያን እንታደግ በቅድስት እስራኤል” በሚል መሪ መልእክት በፔታህ፣ ቲቅቫ፣ በናታኒያ እና በሌሎች ከተሞች የገቢ ማሰባሰቢያ እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡ በመጀመሪያ ዙር የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም 8 ሺህ ዶላር እንደተሰበሰበ የጠቆሙት አስተባባሪዎቹ ለሁለተኛ ዙር በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ 6 ሺህ ዶላር ተሰብስቧል ብለዋል፡፡
እስካሁን ባለው የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብር ላይ ከ14 ሺህ ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ለወገን ጦር ገቢ የተደረገ ሲሆን በቀጣይም ቃል የገቡትን ጨምሮ ሌሎች የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብር እንደሚኖር እና የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡
መረጃውን ያደረሰን በእስራኤል ሀገር የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የአማራ ባለሀብቶች ከአፋር ህዝብ ጎን ስለቆሙ ምስጋና አቀረቡ።
Next article“አሸባሪውና ወራሪውን የትህነግ ቡድን አጥፍቶ የሕዝብን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ሰልጥኖ እና ታጥቆ መሰለፍ ያስፈልጋል” ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ