የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የአማራ ባለሀብቶች ከአፋር ህዝብ ጎን ስለቆሙ ምስጋና አቀረቡ።

308
አዲስ አበባ፡ ጳጉሜን 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መስተዳድር አወል አርባ የአማራ ባለሀብቶች ከአፋር ህዝብ ጎን መቆማቸውን ምስጋና በማቅረብ
የባንዳው የትህነግ ቡድን ወረራ ማንነቱን በግልፅ ያሳየ ነው ብለዋል።
ጥላቻውን ማኒፌስቶው ላይ በግልፅ ያስቀመጠ፣ የአማራውም፣ የአፋሩም፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጠላት ነው። ከኛ የሚጠበቀው ጠላትን ማወቅና ወዳጅን መለየት ብቻ ነው ብለዋል ርእሰ መስተዳደሩ።
ለኛ ትልቁ ጠላት ኢትዮጵያን ለውጪ ጠላትም አሳልፎ ለመስጠት የሚሰራው አሸባሪው ህወሃት ነው ብለዋል።
አፋር ለጦርነት አልተዘጋጀም ብለው ወረውናል፤ አሸባሪው ኢትዮጵያንም እየመራ ሽፍትነት ሲሰራ እንደነበር ገልጸዋል።
“ሀገርን እየመራ ትግራይን ነፃ ስለማውጣት የሚያወራ ጠላት ነው፤ መርዘኛው ቡድን አፋርን በግዞትና በቅኝ ግዛት የመያዝ ህልም አለው፤ አፋር በአፋር ምድር እንዳይኖር የሚሰራ ጠላት ነው፤ ጥፋት እየጨመረ ሲመጣ አይንንም ጆሮንም ልቦናንም ይዘጋል፤ ህወሃት የሆነው እንደዚህ ነው” ብለዋል።
ለመውረር ሲመጡ በዱላና በድንጋይ መሳሪያቸው ተማርኳል ነው ያሉት። ከተደመሰሱትና ከተማረኩት ውጪም ለማምለጥ ሲሮጡ ጎርፍ በልቷቸዋል፤ ውኃችን ግንድና ድንጋይ ሳይሆን የአሸባሪውን አስከሬን ይዞ ይዞራል። ለትግራይ ህዝብ ደንታ ቢስነቱን በተግባር አሳይቷል ብለዋል።
“ሁሉም አፋር ለሀገሩ መከላከያ መሆኑን ያየንበት ነው። እራሱን እኔ ለሀገሬ ጄኔራል ነኝ ብሎ እየተዋጋ ነው። ሁሉም በዚህ መንገድ ማሰብ አለበት። አፋር ለነሱ መጥፊያ ፈንጅ ሆኗባቸዋል” ነው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ።
“የእነሱ ቀሪው ሀብት ምላስ ነው። የሌለ ነገር በሚዲያ ይለፈልፋሉ። የኢትዮጵያ ህዝብ ኀይል ከሁሉም ይበልጣል። እያንዳንዱ ዜጋ በሀገሩ ንጉስ ነው። መከላከያችን መደገፍ አለብን ከስጦታዎች ሁሉ የሚበልጠውን ህይወትን የሚሰጥ እሱ ነው። ሀገር የምትፈርሰው ይህ ተቋም ከፈረሰ ብቻ ነው። የብዙ ሀገሮችን ድምር ህዝብ የምትበልጠው ኢትዮጵያ ለትህነግ አትሸነፍም” ብለዋል።
ጋሊኮማ ላይ ስለተጨፈጨፉት ንጹሃን ትውልድ እንዳይረሳው አድርገን እንሰራለን ነው ያሉት። አፋር የገደለውን ያውቃል። ከጠላቶቻችን የሚበልጠው ጠላት የእኛ ድክመት ነው፤ ምድር ለደካሞች ቦታ የላትም። ጠንክረን መስራት ያድነናል። ትልቁ ወዳጃችን አቅማችን ነው። ጠላት ወዳጅ የሚሆነው አንገት ደፍተህለት ሳይሆን አቅምህን ተጠቅመህ ራስህን ስታስከብር ነው ብለዋል።
“ኢትዮጵያን ለማፍረስ አፋርን እንደመሰላል ለመጠቀም ለፈለገው ቡድን እንደማይታሰብ አሳይተናል። ምክንያቱም እኛ በኢትዮጵያ አንደራደርም። አሁን አፋር ሁሉም ግምባር ላይ ነው። አሸባሪው ቡድን የሚመኛትን መስመር የሚያገኛት በአፋር መቃብር ላይ ብቻ ነው። ትናንትም፣ ነገም፣ ዛሬም የኢትዮጵያ ምሽግ ነን ብለዋል ርእሰ መስተዳድሩ።
ዘጋቢ:–ዘመኑ ታደለ– ከሰመራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበአጣዬ ከተማ ተከስቶ በነበረው የጸጥታ ችግር ቤታቸው ለተቃጠለባቸው 64 አባውራዎች የመኖሪያ ቤት ርክክብ ተደረገላቸው።
Next articleበእስራኤል ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለህልውና ዘመቻው ከ14 ሽህ ዶላር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡