
ደብረብርሃን፡ ጳጉሜን 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በከተማዋ ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች እንዲቋቋሙ አሁንም ቤት የመገንባቱ ሥራ እየተካሄደ መሆኑን የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር አስታውቋል።
በ8 ብሎክ የተገነቡ 64 የመኖሪያ ቤቶች ናቸው ለነዋሪዎች የተላለፉት።
ቤት ንብረታቸው የወደመባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ሁሉም ርብርብ እያደረገ መሆኑን የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ታደሰ ገብረፃዲቅ ተናግረዋል።
በቀጣይም ሁሉንም ዜጎች ለማቋቋም እየተሠራ ነው ብለዋል።
ጊዜያዊ መጠለያዎቹ መሠረተ ልማት ተሟልቶላቸው አገልገሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆን 8ቱ ብሎኮች በ3 ነጥብ 1ሚሊዮን ብር እንደተገነቡና በግንባታውም ከ6 መቶ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ጊዜያዊ የሥራ እድል መፍጠሩን አቶ ታደሰ በርክክቡ ወቅት ተናግረዋል።
የመጠለያ ቤቱ ተጠቃሚ ለሆኑ አካላት የአልባሳትና አስፈላጊ የሆኑ የቤተ ቁሳቁስ እንደተሟላላቸው የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ አገኘሁ መክቴ ገልጸዋል።
የፌደራልና የክልል መንግሥታት የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበትም የ24 መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ዛሬ ተጀምሯል።
በአዲስ የተገነባላቸውና የሚገነባላቸው ወገኖችም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡- ኤልያስ ፈጠነ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ