
ባሕር ዳር፡ መስከረም 18/2012 ዓ/ም (አብመድ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳድር ጋዝጊብላ ወረዳ አስከተማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች በቤተ ክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በማውገዝ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
በቤተ ክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ ጥቃት የሚያደርሱ አካላትን መንግሥት ተጠያቂ እንዲያደርግም ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል።
ፎቶ፦ የጋዝጊብላ ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት