
ባሕር ዳር፡ ጳጉሜን 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገር አቀፍ ደረጃ 5 ሚሊዮን ወጣቶች የሚሳተፉበት “ነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተመንግሥት“ በሚል መሪ መልዕክት የወጣቶች ንቅናቄ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ዩዝ ኢንፓወርመንት ማኅበር እና ሀገር አቀፍ የወጣቶች ንቅናቄ አሰተባባሪ ዓለማየሁ ሰይፉ ገልጸዋል።
ሀገር አቀፍ የወጣቶች ንቅናቄው በኢትዮጵያ ባሉ ወረዳዎች እና ከተሞች ከ5 ሚሊዮን በላይ ወጣች የሚሳተፉበት መሆኑ ተገልጿል።
በሀገር አቀፍ ንቅናቄው የተመለከተ መግለጫ የሰጡት የንቅናቄው አስተባባሪ ወጣት አክሊሉ ታደሰ እንደገለጹት የንቅናቄው ዋና ዓላማ የኢትዮጵያን እውነታ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ማሳወቅ፣ የሽብርተኛው ትህነግን ወረራን ማጋለጥ፣ የሀገር የመጨረሻ መከታ የሆነውን መከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰውን ግፋ ማጋለጥ እና የመንግሥት እና የሕዝብ ትስስር ምን ያህል እንድሆነ ማሳወቅ ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ ደረጃ በየወረዳው እና በየከተማው የፖስታ ማሰባሰቢያ ጣቢያ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑም በመግለጫው ተነግሯል። ንቅናቄው ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥቅም ይኖረዋል ተብሏል፡፡ የፖስታ መልእክቱም ቀጥታ ለፕሬዝዳንት ጆባይደን የሚደርስበት መንገድ ተዘጋጅቷል ተብሏል።
ዘጋቢ፡- ዳንኤል መላኩ- ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ