“የዛሬ ተመራቂዎች ሽብርተኛው ትህነግን ለመፋለም በሕዝብ የተሸኛችሁ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናችሁ ልዩ ያደርገዋል” ኮሎኔል ጌታቸው አሊ የብር ሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ዋና አዛዥ

269
ፍኖተሰላም፡ ጳጉሜን 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለ34ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ምልምል መሠረታዊ ወታደሮች የፌዴራል እና የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ የሥራ ኅላፊዎች በተገኙበት እያስመረቀ ነው፡፡
በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የብር ሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ዋና አዛዥ ኮሎኔል ጌታቸው አሊ “የዛሬ ተመራቂዎች ሽብርተኛው ትህነግን ለመፋለም በሕዝብ የተሸኛችሁ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናችሁ ልዩ ያደርገዋል” ብለዋል፡፡
ኮሎኔል ጌታቸው ለተመራቂ መሰረታዊ ወታደሮቹ ባስተላለፉት መልዕክት ተመራቂዎቹ ሕዝብ መርቆ የሸኛችው ብርቅዬ ወታደሮች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
እናም በትምህርት ቤቱ የተሰጣቸውን የተግባር እና የንድፈ ሐሳብ ትምህርት ሕዝብን እና ሀገርን በማስቀደም እንዲጠቀሙበት አደራ ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ጻዲቁ አላምረው -ከብርሸለቆ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለተፈናቃዮች 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት የምግብ እና አልባሳት ድጋፍ አደረገ፡፡
Next articleየወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ እንደ ንሥር የጠላትን እንቅስቃሴ እየተከታተለ ነው።