
ደሴ፡ ጳጉሜን 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ሽብርተኛው የትህግ ወራሪ ቡድን በፈጸመው ጥቃት ከተለያየ አካባቢ ተፈናቅለው በደሴ ከተማ ተጠልለዉ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሠራተኞችና የሥራ ኀላፊዎች የምግብ እና አልባሳት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፋን በደሴ ከተማ ተገኝተዉ ያስረከቡት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቤል አዳሙ ተቋሙ በአፋር እና በአማራ ክልሎች በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ ድጋፍ ማድረጋቸዉን አንስተዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋምም ያላሰለሰ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አበበ ገብረመስቀል ለተደረገዉ ድጋፍ ምሥጋና አቅርበው በተባበረ ክንድ ይህንን ቀን ማለፍ ይገባል በማለት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ማኅሌት ተፈራ-ከደሴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ